የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

AMN – መስከረም 30/2017

አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ መስከረም 27/2017 ዓ.ም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አምባሳደር ታዬ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ ያለዎት መልክዕክት መላካቸውን ከኅብረቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

መሪዎቹ በመልዕክታቸው ፕሬዚዳንት ታዬ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።

የኳታሩ ኢሚር ሼህ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ለኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አልዎት ያስተላለፉ ሲሆን ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

በኳታር እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት በልማት ትብብር እንደሚጠናከር መግለጻቸውንም ከኳታር ዜና አገልግሎት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ፕሬዚደንት ታዬ አጽቃሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው በመሾማቸው እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ልምዳቸውን ተጠቅመው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግንባታ ላይ ያላትን ሚና እንደሚያሳድጉ እና በዓለም አቀፍ አጀንዳ ላይ ያሉ ችግሮችን እንደሚፈቱ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

በቤላሩስ ዋና ከተማ ሙሳካ እና አዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና የዓመቱ ዲፕሎማሲያዊ ታሪክ ባለፉት 30 ዓመታት ከተከበረው ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን በአፍሪካ እንደ እውነተኛ ወዳጅ እና ደጋፊ እንደሚቆጥሩ እና በለውጡ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ትብብርን ለማሳደግ ፍቃደኛ መሆናቸውን ተናግሯል።

ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ ቤላሩስ ብሪክስን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት ኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓን እንዲቀጥልም ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኤስ.ቢ ኒውስ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review