የቱሪዝም ሚኒስቴር ከዩኔስኮ ጋር በመተባበር መቀመጫቸውን በአዲስአበባ ላደረጉ አምባሳደሮች ባዘጋጀው በዚህ የጉብኝት መርሀግብር ላይ ከ20 በላይ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ::
በጉብኝቱ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም በተመለከተ በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ገለፃ ተደርጎላቸዋል::
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም(ዩኔስኮ) ካስመዘገበቻቸው ዓለም አቀፍ ቅርሶች መካከል አንዱ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ መሆኑን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡