AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ጸሃፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የተመድ ም/ዋና ጸሃፊ አሚና መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በዓመታዊው የተመድ አፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ስብሰባ ላይ ይታደማሉ፡፡
ዳግም የታደሰውን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ህንፃ እንደሚመርቁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።