የተማሪዎች የፈጠራ ሃሳብ ዳብሮና በልፅጎ ሥራ ላይ እንዲውል የተጠናከረ እገዛ እየተደረገ ነው

You are currently viewing የተማሪዎች የፈጠራ ሃሳብ ዳብሮና በልፅጎ ሥራ ላይ እንዲውል የተጠናከረ እገዛ እየተደረገ ነው

AMN- ህዳር 6/2017 ዓ.ም

የተማሪዎች የፈጠራ ሃሳብ ዳብሮና በልፅጎ ሥራ ላይ እንዲውል የተጠናከረ እገዛ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ የፈጠራ ሥራዎች ውድድር አውደ ርዕይ ተጠናቋል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክተር ቀናቱ አንጋሳ (ዶ/ር)፤ በሁነቱ በርካታ የፈጠራ ሃሳቦች ቀርበው የተወዳደሩበትና የልምድ ልውውጥም የተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል።

የተማሪዎች የፈጠራ ሃሳብ ዳብሮና በልፅጎ ሥራ ላይ እንዲውል የተጠናከረ እገዛ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የስቴም ኢነርጂ ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ አቢዮት ላቀው፤ በፈጠራ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለተማሪዎች ውጤታማነት እገዛ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በውድድሩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ይዘው በመቅረብ ከተሸለሙት ተማሪዎች መካከል ከአሶሳ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት መናሂል አህመድ፣ ከወለጋ ዩንቨርሲቲ ሰኚ አየለ እና ከቀለም ስቴም ሴንተር እዮሲያስ ጎሹ፤ በውድድሩ በመሸለማቸው መደሰታቸውን ገልጸው፥ በቀጣይ ለተሻለ ስራ እንደሚዘጋጁም ተናግረዋል።

በፈጠራ ውድድሩ ከመሸለም ባለፈ ሰፊ እውቀትና ልምድ የተጋራንበት መልካም አጋጣሚ ነበር ሲሉም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አውደ ርዕዩ የትምህርት ሚኒስቴር፣ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review