የተሟላ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን በትኩረት እየሰራን ነው – የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት

You are currently viewing የተሟላ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን በትኩረት እየሰራን ነው – የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት

AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተሟላ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን በተያዘው ሀገር አቀፍ የፍትህ ማሻሻያ መሰረት በምክር ቤቱ አፈጉባኤ የሚመራ የፍትህ አካላት ያሉበት አቢይና ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቁሞ ሁሉን አቀፍ የፍትህ ሪፎርም ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር ገለጹ፡፡

የፍትህ ሪፎርሙ አካል የሆኑ ተቋማትም ያከናወኗቸውን አንኳር ተግባራት እና በዕቅድ የያዟቸው ቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር፤ በተናበበ የፍትህ ሪፎርም የተሟላ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ ለሪፎርም ስራው ቁልፍ ሚና ያላቸው ዋና ዋና ስትራቴጂካል ጉዳዮችን የእቅድ አንድ አካል በማድረግ ለተግባራዊነቱ በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

አፈጉባኤዋ አክለው በቀጣይ በፍትህ ተቋማቱ በፍትህ ሪፎርሙ የተሰሩ አንኳር ጉዳዮችን በአካል ምልከታ በማድረግ መሻሻልና መቀጠል ያለባቸውን ስራዎች የጋራ አድርገን በተግባር ምዕራፍ የላቀ የፍትህ ስርዓት ለመፍጠር በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የፍትህ ሪፎርሙ አካል የሆኑ ተቋማት ኃላፊዎች በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን የፍትህ ስርዓት ለመፍጠር በፍትህ ማሻሻያው ዘመናዊ መዋቅር ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም አዲስ አበባን ሰላሟና ደህንነቷ የተረጋገጠ፣ የተሟላ የፍትህ ስርዓት ያለባት ከተማ ለማድረግ እንሰራለን ማለታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review