AMN- መስከረም 20/2017 ዓ.ም
በሰፋት ያልተዋወቁ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የውሃ ላይ ቀዘፋ፣ የተራራ ላይ የብስክሌት እና የእግር ጉዞ ጉብኝት ተካሂዷል።
ጉብኝቱ በስፋት ያልተዋወቁ መዳረሻዎችን ከማስተዋወቅ ባሻገር በመዳረሻዎች አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደረግ ነው ተብሏል።
መዳረሻዎቹ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት በጉራጌ ዞን መንቆረ እና ሐዋሪያት ዙሪያ የሚገኙ ምቹ ማራኪና ሰላማዊ የጉብኝትና የጉዞ መዳረሻ ሲሆኑ በተለይ የተራራ ላይ የብስክሌት ጉዞ፣ የእግር ጉዞ እና የውሃ ላይ ቀዘፋ ለማድረግ የሚያስችል አስገራሚ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች መሆናቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አመልክቷል።
የጉዞና ጉብኝት መርሃ ግብሩ የቱሪዝም ሚኒሰቴር ከራይድ ዘሪፍት የቱር ማህበራት ጋር በጥምረት የተካሄደ መሆኑን ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።