የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃ እናደርጋለን ያልነዉን ፈጽመን ለዓለም ያሳየንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነዉ-ፕሮፌሰር መኮንን አያና

You are currently viewing የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃ እናደርጋለን ያልነዉን ፈጽመን ለዓለም ያሳየንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነዉ-ፕሮፌሰር መኮንን አያና

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 7/2016 ዓ.ም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን የደረሰበት ደረጃ እናደርጋለን ያልነዉን ፈጽመን ለዓለም ያሳየንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነዉ ሲሉ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የዉሃ ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር መኮንን አያና ገለጹ፡፡

ተመራማሪው ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር ባደረጉት ቆይታ የግድቡ ግንባታ አሁን ትልቅ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም ይፈጥራል ያሉት ፕሮፌሰሩ ለሀገር ዉስጥ ሀይል ፍላጎታችንም የማይተካ ሚና እንዳለዉ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን በያዘችዉ አቋምና በዉስጥ አቅም ይህንን ግድብ ገንብታ ካጠናቀቀች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተፈላጊነት ከመጨመር አንፃርም የራሱ ሚና እንዳለዉም አንስተዋል፡፡

የህዳሴ ግድብ ከሀይል አመንጪነት ባሻገር ትልቅ የዲፕሎማሲ መሳርያ ሆኖ እንደሚያገለግልም ፕሮፌሰሩ ጠቁመዋል፡፡

ይህ ከጫፍ የደረሰው የጋራ ሀብትን ለማጠናቀቅ አሁንም የጋራ ርብርብ ስለሚያስፈልግ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰኚ ታደሰ

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

1 Review ( 4 out of 5 )

Bayisa - bybayisa8@gmail.com
4

Review testing

I appreciate

Write a Review