AMN- ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ባለሙያዋ ሙስና ስትፈፅም እጅ ከፍንጅ ተይዛ ዛሬ በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡
ለከንቲባ ጽ/ቤት በደረሰ ጥቆማ መሰረት የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለሙያ የሆነችው አማረች በላቸው ማሞ ለግብር ከፋይ ግለሰብ ክሊራንስ ለመስጠት በ100,000 (አንድ መቶ ሺ) ብር ጉቦ ስትደራደር በደረሰ ጥቆማ መሰረት ክትትል በማድረግ 50,000(ሃምሳ ሺ) ብር ቢሮ ውስጥ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዛ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡