የቴክኖሎጂ እድገቶች ከአቅም በላይ ለሆኑ ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ እያስገኙ ነው-ዶክተር ባይሳ በዳዳ

You are currently viewing የቴክኖሎጂ እድገቶች ከአቅም በላይ ለሆኑ ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ እያስገኙ ነው-ዶክተር ባይሳ በዳዳ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

የቴክኖሎጂ እድገቶች ከአቅም በላይ ለሆኑ ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ እያስገኙ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሽፕ 2025 ውድድር በሳይንስ ሙዚየም ተጀምሯል።

በማስጀመሪያው መርሃ ግብር የተገኙ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ እንደገለፁት፤ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ ሚና ያላቸውን የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳቦችን ለማጎልበት የሚያስችል ምቹ ምህዳር መፈጠሩን ተናግረዋል። የቴክኖሎጂ አድገቶች ከአቅም በላይ ለሆኑ ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ እያሰገኘ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ሮቦቲክስ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያሉ ቴክኖሎጂዎች ለሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን አስታውሰው

ኢትዮጵያ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማስመዝገብ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራች ነው ብለዋል።

የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት በዲጂታል ዘርፍ ምቹ ምህዳር ለመፍጠር መሰራቱን አንስተው ይህም በዘርፉ ያለውን ክህሎትና እውቀት ለማዳበርና የፈጠራ ሃሳብን ለማበርከት ማገዙን ጠቁመዋል።

የዲጂታል መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የግሉ ዘርፍ ለዲጂታል ልማት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሚያስችል ምህዳር መፈጠሩን ተናግረዋል።

ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ ፣ ሂሳብና ምህንድስና ትኩረት በመስጠት ከትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነውም ብለዋል።

የአፍሪካ ሮቦቲክስ ውድድር ፈጠራን የሚደግፉ ስራዎች የሚታዩበት እንደሆነና ሃሳብን በማልማትና በማሳደግ እንዲሁም ወደተግባር በመለወጥ ሀብትና የስራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

የኢትዮ ሮቦቲክስ የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናክሬም መኮንን በበኩላቸው፤ ውድድሩ የተማሪዎችን የፕሮግራሚንግ፣ ዲዛይን፣ ምህንድስና እና ተዛማጅ ክህሎቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ የመንግሥት፣ የግልና የዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል። ተወዳዳሪዎችም ውድድሩን ለማሸነፍ የሚያስችላቸው ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review