የትምህርት ፖሊሲውን ባልተከተለ መልኩ የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን:- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

You are currently viewing የትምህርት ፖሊሲውን ባልተከተለ መልኩ የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንወስዳለን:- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

AMN- መስከረም 7/2017 ዓ.ም

የትምህርት ፖሊሲውን ባልተከተለ መልኩ የሚያስተምሩ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

ለዜጎች የትምህርት ሽፋንን በስፋትና በጥራት ለማዳረስ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ተቀርፆ በመተግበር ላይ ሲሆን ለዚህም መንግስት፣ አጠቃላይ ባለ ድርሻ አካላትና ወላጆች ጭምር ትብብርና ተሳትፎ እያደረጉ ነው።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፤ በመዲናዋ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከቅድመ-መጀመሪያ እስከ መሰናዶ ደረጃ በርካታ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን አክብረው የመማር ማስተማር ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የተወሰኑ የግል ትምህርት ቤቶች ከትምህርት ፖሊሲውና ከስርዓተ ትምህርት ማዕቀፉ ባፈነገጠ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደት እየተከተሉ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል።

በመሆኑም በእንዲህ አይነት ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ተከታትለን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ ተናግረዋል።

በመዲናዋ በርካታ የግል ትምህርት ቤቶች ብዙ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች እያስተማሩ መሆኑን ጠቅሰው በሂደቱ ህግና ስርዓትን መከተል ግዴታቸው እንደሆነ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review