የትግራይን ህልውና ለማረጋገጥ ለለውጥ የሚንቀሳቀስ ኃይል አካል ነኝ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

You are currently viewing የትግራይን ህልውና ለማረጋገጥ ለለውጥ የሚንቀሳቀስ ኃይል አካል ነኝ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

AMN – ግንቦት 13/2017 ዓ.ም

ሁሉንም ሰላማዊ መንገድ በመጠቀም የትግራይን ህልውና ለማረጋገጥ ለለውጥ የሚንቀሳቀስ ኃይል አካል ነኝ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል፡፡

የፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ዋና ተደራዳሪ የነበሩት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የቀድሞው ህወሃት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲወጣ ማድረግ እና ወደ ምርጫ ቦርድ ስርዓት መግባት የፕሪቶሪያው ስምምነት አካል እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ቢወስድም ጉባኤ ማድረግ ባልፈለጉ ጥቂት አካላት ምክንያት እንዲሰረዝ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የሰላምን መንገድ አሟጠው ሳይጠቀሙ ለተወሰኑ ሰዎች የስልጣን ፍላጎት ሲባል ህዝብ ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድ የህወሃትን መንገድ በመስበር የራሱን መስመር መምረጥ እና እኛ ያልነው ብቻ ካልሆነ ከሚሉ አካላት ራሱን መጠበቅ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

በእኔ መፈክር ሌላ ወጣት ተጨማሪ ዋጋ እንዲከፍል አልፈልግም ያሉት ሚኒስትሩ የፕሪቶሪያው ስምምነትም ይህንን የሚያስቀር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ሁሉንም ሰላማዊ መንገድ በመጠቀም የትግራይን ህልውና ለማረጋገጥ ለለውጥ የሚንቀሳቀስ ኃይል መኖሩን በመግለጽ ይህንንም በተደራጀ መልኩ ማካሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ እኔም የዚህ አካል እሆናለው በማለት አረጋግጠዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review