የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መድቧል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መድቧል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መመደቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መቅረፍ የሚቻለው ምርታማነትን በመጨመር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መመደቡንም አስታውቀዋል፡፡

ማዕድ ማጋራት፣ ትምህርት ቤት ምገባ እና እሁድ ገበያ መንግስት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ የሚያደርገው ጥረት አካል መሆኑን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ባለሃብቶችን በማስተባበር ባከናወነው ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ 249 ሺህ አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም የዋጋ ንረቱን አሁን ላይ ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ የተቻለ መሆኑን በመግለጽ ይህንን ወደ ነጠላ አሃዝ ማውረድ የመንግስት ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review