የናይል የትብብር ስምምነት ተፈጻሚ መሆን የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን ለመመስረት ያስችላል – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

You are currently viewing የናይል የትብብር ስምምነት ተፈጻሚ መሆን የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን ለመመስረት ያስችላል – የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር

AMN – ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምንት ትናንት ጥቅምት 3 ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) የናይል የትብብር ስምምነት ወደ ተግባር መግባትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

የናይል የውሃ ሀብቶች አጠቃቀም እና የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ወደ ተግባር መግባት ኢትዮጵያ በጋራ ለረዥም ዓመታት ስትለው የነበረው የአባይ ወንዝ ውሃን በፍትሃዊነትና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የትብብር ማዕቀፉ በአጠቃላይ 15 ዋና ዋና መርሆዎች ያሉት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ 4ቱ በጋራ የመጠቀም መብት ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን የያዙ፣ ሌሎች ደግሞ የመጠበቅ፣ የመንከባከብና ሌሎች ጉዳዮችን የያዙ ናቸው ብለዋል።

በ45 አንቀጾች የተከፋፈሉ ሆነው የተለያዩ ህግና ማዕቀፎች ያሉት ይህ የትብብር ማዕቀፍ ኢ-ፍትሃዊ የቅኝ ግዛት ዘመን የውሃ ውሎችን የሚያስቀር ነው ብለዋል።

የናይል የትብብር ስምምነት ተፈጻሚ መሆን የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን ለመመስረት ያስችላል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኮሚሽኑ ለሁሉም ተጠቃሚነት የናይል ወንዝን የማስተዳደርና የመጠበቅ ኃላፊነት እንደሚወስድም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ በጋራ ለመልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር አሁንም አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም አክለዋል፡፡

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review