የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ ነው-ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

You are currently viewing የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ ነው-ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

AMN – ታኀሣሥ 21/2017 ዓ.ም

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ መሆኑን ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ወቅቱ የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት የመጨረሻ ቀናቶች ላይ የሚገኝ በመሆኑ የንግዱን ማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲባል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዲሁም የተወሠኑ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሠኞ- ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 የኦንላይን የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኙ የሚኒስቴሩ መረጃ ያሳያል፡፡

በመሆኑም የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት በበጀት ዓመቱ ከሀምሌ 1/2016 እስከ ታህሳስ 30/ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለቅጣት የሚታደስ መሆኑን ያስታወሰው ሚኒስቴሩ ከሠኞ እስከ ቅዳሜ እስከ ምሽቱ 2፡30 በሚሰጠው የኦንላይን አገልግሎት የንግዱ ማህበረሰብ አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት የንግድ ስራ ፈቃዱን አስቀድሞ እንዲያድስ አሳስቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review