የአህጉራችንን የፀጥታና ደህንነት ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ትብብራችንን ማጠናከር ወሳኝ ነው- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የአህጉራችንን የፀጥታና ደህንነት ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ትብብራችንን ማጠናከር ወሳኝ ነው- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች ያሻሉ

ዛሬ “አፍሪካ፤ በጠንካራ አንድነት፣ ለሁለንተናዊ ፀጥታና ሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ አትኩሮቱን ባደረገው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ታድመናል ብለዋል ፡፡

የአህጉራችንን የፀጥታና ደህንነት ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ትብብራችንን ማጠናከር ወሳኝ ነው።

ለዚህም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የሚለውን አህጉራዊ መርሃችንን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል።

የአህጉራችንን ችግሮች ሌሎች እንዲፈቱልን መጠበቅ የለብንም።

ጠንካራ አጋርነት በመፍጠር የተሻለ ወታደራዊ አቅም የመገንባት እና በመላው አፍሪካ ሰላምን የማረጋገጥ ጉዳይ ምኞት ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ይልቁን ለዘላቂ ዕውንነቱ በአዲስ መንፈስ በቁርጠኝነት መነሳት አለብን።

ይህንን አፍሪካዊ ጉባኤ በማሰናዳቱ ረገድ ቁልፍ ሚና ለተወጡት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል አቶ ተመስገን በመልእክታቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review