የአማራ እና የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊዎች ከሰጡት መግለጫ የተቀነጫጨቡ መልዕክቶች

You are currently viewing የአማራ እና የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊዎች ከሰጡት መግለጫ የተቀነጫጨቡ መልዕክቶች

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ

-የጋራ ትርክትን ለሁሉም ማስረፅ የብልፅግና እሴቶች ናቸው፤

-እስረኞችን ከመፍታት፣ ከሀገር ለቀው የተሰደዱትን እስከመመለስ ድረስ ዜጎች ነፃነትን እንዲለማመዱ በማድረግ የተወሰዱ እርምጃዎች የዴሞክራሲ ምህዳር ክፍት የተደረገባቸው ከፍተኛ እርምጃዎች ናቸው፤

-ብልፅግና በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ለማስተካከል ቃል የገባቸውን ጉዳዮች መፈፀም የቻለ ብሎም ባህል ያደረገ ፓርቲ ነው፤

-ዕዳ እና ብድር ላይ መሠረት ያደረገውን እና የአመራር ብስለት ጉድለት የነበረበትን ያለፈ የኢኮኖሚ ሥርዓት የተካው ብልፅግና፣ ባለፉት አምስት ዓመታት አዳዲስ እና ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ፈጥኖ በመጨረስ ሰው ተኮር ተግባራት ከፍ ባለ ተነሳሽነት ሰርቷል፤

-የሰላም መስፈን እና የሰላም ግንባታ ለሁሉም ነገር መሠረት ነው፤

-የጋራ ትርክት ግንባታ ላይ መሠረት ያደረገ የሰላም ማስፈን፣ የሰላም ግንባታ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፤

-እንደ ሀገር በተለያዩ አካባቢዎች በነጠላ ትርክት ውስጥ ያሉ የፅንፈኞችን ድርጊት ለማክሰም ብሎም ለማጥፋት ፓርቲው የተደራጀ የአሰራር ሥርዓት ዘርግቷል፤

-ፅንፈኝነት እና እኔ ብቻ አውቃለሁ የሚለው አስተሳሰብ ኋላ ቀርነት ነው፤

-ብልፅግና ፓርቲ ከዚህ ቀደም ብሔር ተኮር ብቻ ተደርጎ የተገነባውን የነጠላ ትርክት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሟሸሸ እና እየከሰመ እንዲሄድ፣ ይልቁንም ስለ አንድ ትልቅ ሀገር እንድናስብ እያደረገ የሚገኝ ፓርቲ ነው፤

-ብልፅግና ፓርቲ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ እሴቶች እና በጋራ የተሰሩ ታሪኮች ትልቅ ሀብቶች እንደመሆናቸው መጠን በእኩልነት ተከብረው እና ተጠብቀው በጋራ ለአንድ የበለፀገች ሀገር ለመስራት እያደረገ ያለው አስተዋፅዖ ቀላል የሚባል አይደለም፤

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ

-ብልፅግና ፓርቲ የተከተለው መርህ ኢትዮጵያ የነበረችበትን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ በመገንዘብ እንደ ከዚህ ቀደሙ አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመር ሳይሆን ከበፊቱ ጥሩ የነበሩት በማስቀጠል የተበላሹትን ደግሞ የማሻሻል እሳቤ ነው፤

-ብልፅግና ፓርቲ ይዞት የመጣው የመደመር እሳቤ በሀገሪቱ ውስጥ የነበረውን የፖለቲካ ስብራት የጠገነ እና ከግንባር ወደ አንድ ህብረብሔራዊ ፓርቲ ማምጣት ያስቻለ ነው፤

-የሀሳብ ልዕልናን ያስቀደመ ስልጡን የፖለቲካ ባህል ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ምቹ መደላድል ይፈጥራል፤

-የዴሞክራሲ ስነ-ምህዳርን ለሀሳብ ነፃነት እና ለሀሳብ እኩልነት ክፍት ማድረግ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ አንዱ ማሳያ ነው፤

-ኢትዮጵያን ሊያሻግር እና ሊያሰባስብ የሚችለው ትርክት ብሔራዊነት ነው፤

-በመደመር መንገድ ብሔራዊነትን ትርክት አድርገን ኢትዮጵያን ልናሻግር እንችላለን፤

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review