-በጤናው ዘርፍ ህፃናት ላይ የተሰራው ሥራ በተለይም የቀዳማይ ልጅነት መርሐ-ግብር በሚል ከቅድመ ወሊድ ጀምሮ ለእናቶች እንክብካቤ የማድረግ እና ህፃናት ከተወለዱም በኋላ ዘርፈ ብዙ ክትትል በማድረግ ህፃናትን የቀጣዩ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የማድረግ ሥራ ውጤት የተገኘበት ነው፤
-የቀዳማይ ልጅነት መርሐ-ግብር ከአዲስ አበባ ጀምሮ በክልሎች እየሰፋ መጥቶ በአማራ ክልል ከተሞችም እየተከናወነ ያለ ሥራ ነው፤
-በትምህርት ዘርፍም የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ውጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል፤
-ለወጣቶች መዋያ እና መዝናኛ ሥፍራዎች፣ ሀሳባቸውን የሚያንሸራሽሩበት ቦታዎች ላይ እየተከናወነ ያለው ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው፤
-ቀደም ሲል ወጣቶች ሀሳባቸውን ወደ ውጤት፣ ወደ ቢዝነስ የሚቀይሩበት ዕድል ያልነበረ ሲሆን፣ አሁን ይሄ ዕድል ተመቻችቷል፤
-በሀገር ደረጃ ወጣቶች ሀሳባቸውን ወደ ውጤት ቀይረው እዛ ሀሳባቸው ላይ ኢንቨስት ከሚያደርጉ ባለሀብቶች ጋር የሚገናኙባቸው የተለያዩ ቦታዎች አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ተቋቁመዋል::