የአሜሪካው ቪዛ ባንክ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጣናው ዓለም አቀፍ የሃዋላ አገልግሎትን የማስፋት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአሜሪካው ቪዛ ኢንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ አገልግሎት ኩባንያ ጋር በሃዋላ፣ በዲጂታል ፋይናንስና በአዳዲስ የትብብር ዕድሎች ላይ በጋራ ለመስራት ተወያይተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሹሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግስት በእኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የዲጂታላይዜሽን ትብብር እንዲጎለብት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።
የቪዛ ኢንክ የደቡብና ምስራቅ አፍሪካ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት ሚካኤል በርነር ዓለም አቀፍ የቪዛ አገልግሎትን በኢትዮጵያ እና በቀጣናው ሀገራት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያን አጠቃላይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ እንዲሁም የዲጂታል ስትራቴጂ ፕሮጀክቶች እና የትግበራ እቅዶችን አስመልክቶ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።