የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እንሰራለን – አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እንሰራለን – አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN – የካቲት 18/2017 ዓ.ም

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለመደገፍ እና የአሰራር ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል ውይይት፣ ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር መደረጉ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱም አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍና ዘርፍን በሲስተም ለመምራት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡

አቶ ጃንጥራር አክለውም የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከባለድርሻ አካለት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በትኩረት እንሰራለን ብለዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው ጉምሩክ ኮሚሽን የተሻለ አሰራር መዘርጋቱን ጠቅሰው የሲስተም አለመኖር፣ ብልሹ አሰራር እና አየር ባየር ነጋዴዎች ላይ ክትትል አለማድረግ እንቅፋት እንደሆነባቸው መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያማክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review