የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የጎለበቱ ሙያተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ::
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለ2ኛ ጊዜ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ 127 ሙያተኞቹን አስመርቋል::
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የጎለበቱ ሙያተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል ገልጸዋል::
አዲስ አበባ ከተማ በእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁት ኢንጂነር ወንድሙ፣ ይህንን የሚመጥን የሰዉ ሃይል ለመገንባት እየተሰራ ነዉ ብለዋል::
በስልጠናው ከወረዳ እስከ ከማዕከል የሚገኙ የኤጄንሲው ባለሙያዎች መሳተፋቸውም ተመላክቷል።
በቴዎድሮስ ይሳ