AMN – ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞች እየተተከሉ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ በ2018 በአጠቃላይ 50 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ እየሰራች ነው፡፡
በዘንድሮው ዓመት የተተከሉ ችግኞችን ቁጥር 40 ቢሊየን ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው ።
በዘርፉ በተከናወኑ ስራዎች የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 23.6% ደርሰዋል፡፡
በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ የደን ሽፋኑን 30% ለማድረስ እየተሰራ ነው።
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስካሁን 6.9 ቢሊየን ችግኞች ተተክለዋል ።
ዛሬ ከማለዳ 12:00 እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት ቀኑን ሙሉ ለሚከናወነው የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞች የመትከሉ ተግባር ተጀምሯል፡፡
ለአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በሁሉም ክልሎች 8 ሺህ 452 ካርታ የወጣላቸው ቦታዎች ተዘጋጅተዋል፡፡
ለአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ 317 ሺህ 521 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል ፡፡
አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊዎች ከ10 በላይ ችግኝ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንደሚገልጡም ይጠበቃል፡፡
የተዘጋጁት ቦታዎች አጠቃላይ ስፋትም 317 ሺህ 521 ሄክታር ነው ፡፡
2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ የተዘጋጀ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 1 ሚሊየን ሄክታሩ ካርታ የተዘጋጀለት ነው፡፡
በአዲስ አበባ ለሚከናወነው የአንድ ጀምበር 6 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የሚተከሉ ችግኞችና ቦታዎች በጥናት ተለይተው 158 ቦታዎች 396 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል ፡፡
በመርሃግብር 20 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስካሁን 16.1 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል ፡፡
ባለፈው ዓመት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 89 በመቶ የሚሆኑት መፅደቃቸው በጥናት ተረጋግጠዋል።
መረጃው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮና የግብርና ሚኒስቴር
በሽመልስ ታደሰ