በአብሮነት እና በማካፈል የሚደምቀው በዓል
ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓለም ዙሪያ በእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ የእርድ ወይም የመስዋዕትነት በዓል በመባልም ይታወቃል፡፡ ነብዩ ኢብራሂም ከረጅም ጊዜ በኋላ በአሏህ ፈቃድ ወንድ ልጅ ተቸራቸው፡፡ ልጃቸው ኢስማኤል ለአባቱ ታዛዥ እንደነበርም የኃይማኖቱ አስተምህሮ ያስረዳል፡፡
ይሁን እንጅ ነብዩ ኢብራሂም በደስታቸው ማግስት የእምነታቸው ጽናት የሚፈተንበት ወቅት ተፈጠረ። አንድያ ልጃቸውን መስዋዕት ያደርጉ ዘንድ ከፈጣሪ ታዘዙ፡፡ የልጃቸው ፍቅር ቢያስጨንቃቸውም ትዕዛዙ የፈጣሪያቸው ነውና ሊፈጽሙ ወደ አረፋ ተራራ ወጡ፡፡
ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ሊሰው ሲዘጋጁ ከሰማይ በኢስማኤል ምትክ መስዋዕት የሚሆን በግ ወረደላቸው፡፡ ይህንን ኃይማኖታዊ አስተምህሮ መነሻ በማድረግ በዓሉም ኢድ አል አድሃ (አረፋ) እየተባለ በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡
ኡስታዝ መሀመድ ፈረጅ በአዲስ አበባ አየር ጤና አካባቢ በሚገኘው የአንሷር መስጅድ አስተማሪ ናቸው፡፡ ኡስታዙ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ላይ ኃይማኖታዊ ትምህርት በመስጠት እና ሃሳባቸውን በመሰንዘር ይታወቃሉ፡፡
እንደ ኡስታዝ መሀመድ ፈረጅ ገለጻ የዒድ አል አድሃ በዓል ነ?? ????? ????? ?????? ???? ??? ?? ???? ???? ???? ?????? ?? ?????? ????? ??? ?? ???? ???? ??? ??? ??? ????? ????? ?????? ?? ??? ???? ????
????? ??? ??? ????? ????? ???? ?????? ??? ??? ???? ??? ?? ?????? ??? ??? ?ብዩ ኢብራሒም ልጃቸውን ኢስማኤልን በአረፋ ተራራ ላይ በአላህ ትዕዛዝ ሊሠውት የነበረበት ቀን ለማስታወስ የሚከበር በዓል ነው ይላሉ። ኡድህያ ወይም እርድ ግዴታ የሆነበት አንደኛው መልዕክትም ወደ አላህ መቃረብ ነው፡፡
ተከታዮቹ ለእሱ ታዛዥ እንዲሆኑ የተለያዩ ትዛዛት ይሰጣል፡፡ ይህም አንዱ ኡድህያ ማዘዙ ነው ብለዋል፡፡ ይህም እረዱ ብሎ ያዘዘው የዙልሂጃ ወር 10ኛው ቀን ላይ ነው ይላሉ፡፡ ይህም በተለምዶ በሀገራችን አረፋ በዓል የሚባለው ነው። ትክክለኛ ስሙም ዒድ አል አድሃ ነው ይላሉ፡፡ የእርድ፣ የመስዋዕትነት በዓል እንደሚባልም ኡስታዝ መሀመድ ይናገራሉ፡፡
እንደ ኡዝታዝ መሀመድ ገለጻ የዒድ አል-አድሃ ታሪካዊ ዳራ ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን ለአላህ ለመስዋዕት ያደረጉት ቁርጠኝነት የተሞላበት ውሳኔ እና ለመስዋዕትነት የቀረበው ልጅ ያሳየው የተለየ ጽናት ነው፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም የበኩር ልጃቸው የሆነውን ኢስማኤልን ያገኙት በእርጅና ዘመናቸው ነው። ሚስታቸው ሳራ ለፍሬ ባለመብቃቷ አላህ ያለ ዘር አታስቀረኝ፤ እኔን የሚተካ ልጅ ስጠኝ በማለት ዱዓ አደረጉ፡፡ በዚሁ መሰረት በሳራ ፈቃደኝነት ሐጀራ የምትባለውን የቤት ሰራተኛቸውን አገቡ።
ሐጀራም ኢስማኤል የተባለ ልጃቸውን ወለደችላቸው፡፡ ይህ ልጅ በአላህ ፈቃድ በመካ ከተማ እንዲያድግ የተወሰነ ስለነበረ ኢብራሂም ሐጀራን እና ኢስማኢልን ወደ ዐረቢያ ከተማ ወሰዷቸው፡፡ በጣም የሚወዱት ልጃቸው ኢስማኤል ካደገ በኋላ ደግሞ አላህ ልጅህን እንድትሰዋ ታዘሃል የሚል በህልማቸው አሳያቸው፡፡ የነቢያት ህልም ደግሞ ከራዕይ የሚቆጠር ነው፡፡
ስለዚህ ኢብራሂም በህልማቸው ያዩትን በዝምታ አላለፉትም፡፡ በወቅቱ የሆነውን ቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ይተርካል፡፡ “ከርሱ ጋር ለስራ በደረሰ ጊዜም ልጄ ሆይ! እኔ በህልሜ የማርድህ ሆኜ አይቻለሁ፤ እስቲ አንተም ነገሩን ተመልከት፡፡ ምን ይታይሃል አለው። ልጁም አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ፈጽም፤ አላህ ቢሻ እኔን ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ አለው፡፡ የፈጣሪን ትዕዛዝ በትዕግስት ነው የምቀበለው፤ ለዛውም አንተ ታዝዘህ እቀበለዋለሁ አለው፡፡”
አባትና ልጅ በዚህ መንገድ ከአላህ የተላለፈውን ትዕዛዝ ሊፈጽሙ ተነሱ፤ ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸውን እንዲሰው የታዘዙት ከዐረፋት መሬት ብዙም ባልራቀ ቦታ ላይ ስለነበረ ወደዚያው ጉዞ ጀመሩ፡፡
ኢብራሂም ኢስማኤልን ሊያርዱት አጋደሙት፡፡ ልጁም ምንም ሳያንገራግር ከመሬቱ ላይ ተኛ፡፡ ኢብራሂም ልጁን ሊያርዱት ሲሞክሩ ግን ቢላዋው አላርድ አላቸው፡፡ ኢብራሂም እንደገና ቢላዋውን ገዘገዙት፡፡ ነገር ግን ቢላዋው ፈጽሞ ዶለዶመ፡፡ ቢላዋው አልቆርጥ አለ፡፡
ልጁ የሆነው ነገር አልገባውም። አባቱ ቶሎ ስላላረደው ተገረመና አባዬ “ምናልባት የአባትነት ፍቅር ይዞህ ይሆናል በቶሎ ያላረድከኝ፤ እስቲ ዐይኔን በጨርቅ ሸፍነውና እርዱን ሞክር የሚል አስተያየት ሰጠ፡፡ “በዚህን ጊዜ ግን ከወደ ሰማይ ጥሪ መጣ፡፡ የአላህ መልአክ ኢብራሂም ታላቅነትህን አስመስክረሃልና፤ የአላህን ፍቅር ተግብረሃል፤ የታዘዝከውን ትዕዛዝ ፈጽመሃልና እርዱን አቆየው” በማለት አወጀ፡፡
በምትኩም ጅብሪል ከገነት ያመጣውን ሙክት በግ እንዲያርድና ልጁን ወደቤቱ እንዲወስደው ነገረው፡፡ በዚህም መሰረት ሙክት በጉ ታረደ፡፡ ኢብራሂምና ኢስማኤል ወደ መካ ከተማ ተመለሱ፡፡ ሁለቱ ሰዎች ለፈጣሪ መታዘዝን በግልጽ ያሳዩባት ያቺ ዕለት የዒድ አል-አድሃ በዓል ሆና እንድትከበርም ተወሰነ። ኢስማኤል ለመስዋዕትነት የቀረበበት ድርጊት ደግሞ በዚሁ ዕለት የሚታረደው “ኡድሒያ” መነሻ ሆነ በማለት ኡስታዝ መሀመድ ያብራራሉ፡፡ በሂጅራ አቆጣጠር የመጨረሻው ወር ዙል ሂጃህ በ10ኛ ቀን የኢድ ሶላት ከተሰገደ ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ጸሐይ እስክትጠልቅ ድረስ እርድ ማረድ ይቻላል ብለዋል፡፡
ዒድ አል-አድሃ የመስዋዕትነትና የመዳን በዓል ነው፡፡ የሐጅ ጸሎት የሚፈጽም ሰው በዚህ ዕለት ኡድሒያ የማረድ ግዴታ አለበት ይላሉ ኡስታዝ መሀመድ፡፡ ይህ የሚታረደው እርድ መስፈርቱ ጠንካራ ነው የሚሉት ኡስታዝ መሀመድ የሚታረደው በግ፣ ፍየል፣ ከብት አይኑ ሸወርዋራ ያልሆነ፣ አይኑ ያልጠፋ፣ ጀሮው ያልተቆረጠ፣ ቀንዱ ያልተሰበረ፣ እግሩ አንካሳ ያልሆነ፣ በሽተኛ ያልሆነ፣ ያልከሳ መሆን ይኖርበታል፡፡
በችግር ምክንያት ማረድ ላልቻሉ በማረድ ማከፋፈል ይገባል፡፡ አንድ አባወራ ካረደ ለሙሉ ቤተሰብ እንዳረደ ይቆጠርለታል፡፡ በእርድ ወደ አላህ መቃረብ ነው የሚሉት ኡዝታዝ መሀመድ አባወራው ካረደ ልጅ፣ ሚስት እና እሱ የሚያስተዳድራቸው ቤተሰብ በሙሉ ወደ አላህ በዚህ እርድ ተቃርበዋል ማለት ነው ይላሉ፡፡ ቤተሰብን የምታስተዳድረዋ ሴት ከሆነች በእሷ ገንዘብ ተገዝቶ እርዱ ከቀረበ እሷም ምንዳውን ታገኛለች በማለት ያስረዳሉ፡፡ እርድ የሚፈጽሙ ሁሉ ምንዳውን ያገኛሉ ብለዋል፡፡
ይህን እርድ የሚያርደው ሰው ዙልሂጃወር ከገባበት ቀን ጀምሮ ጸጉሩን፣ ጥፍሩን አይቆረጥም፡፡ እርዱን ካረደ በኃላ ነው ጸጉሩን፣ ጥፍሩን የሚቆረጠው ይላሉ፡፡ ይህም ቢላዋውን ይዞ እርድ የሚፈጽመው ሰው ሳይሆን በዋናነት ለእርዱ ወጪ ያወጣውን ለማለት መሆኑን ኡስታዝ መሀመድ ይገልጻሉ፡፡
የቻለ ሁሉ ማረድ እንዳለበት ኃይማኖታዊ አስተምህሮው ያስረዳል። ያልቻለ ሰው ግን ነብዩ አርዶለታል። አንድ ሰው ሁለትና ከዚያ በላይ ማረድ ይጠበቅበታል፣ በማለት ብዙ የእርድ መስዋዕት ባቀረበ ቁጥር ምንዳ ሃጂር እየበዛ ይሄዳል ብለዋል፡፡ በሀገራችን ብዙ ማረድ እምብዛም ባይለመድም በቱርክ ሀገር የሚገኙ ሙስሊሞች ግን ብዙ እርድ እንደሚፈጽሙ ኡስታዝ መሀመድ ይናገራሉ፡፡
እንደ ኡስታዝ መሀመድ ገለጻ ታዲያ ኡድሒያው፣ ኡድሒያ ተብሎ የሚመዘገብልን እርዱም ሆነ አጠቃቀሙ ነቢዩ ያስተማሩትን መንገድ የተከተለ ከሆነ ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች ፍየሉን ያርዱና ለበዓል የሚሆናቸውን ያህል ካስቀሩለት በኋላ ሌላውን ወደ ፍሪጅ ውስጥ ይከቱታል። ይህ ግን ራስን መጋበዝ ነው እንጂ ኡድሒያ ተብሎ አይመዘገብም፡፡
ነቢዩ እንዳስተማሩት ለኡድሒያ ከታረደው ስጋ አንድ ሶስተኛው በቀጥታ ለድሆች መከፋፈል አለበት። የቀረው ብቻ ነው ለቤተሰብ አገልግሎት የሚውለው፡፡ ስለዚህ በዚህ እለት የሚፈጸመው መስዋዕት ኡድሒያ ሆኖ እንዲመዘገብልን ካሻን ያላቸው ለሌላቸው በመስጠት ትክክለኛውን የአስተምህሮ መንገድ መከተል አለብን ይላሉ ኡስታዝ መሀመድ፡፡
በይግለጡ ጓዴ