የአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ የሚተከልበት መርሀ ግብር በይፋ ተጀምሯል፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን

You are currently viewing የአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ የሚተከልበት መርሀ ግብር በይፋ ተጀምሯል፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን

AMN – ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

በዛሬው እለት በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ የሚተከልበት መርሀ ግብር በይፋ መጀመሩን አስመልክተው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡

በመላው ሀገሪቱ ያሉ ዜጎች ከጀንበር መውጣት ጋር ከቤታቸው ወጥተው ወደ መትከያ ቦታዎች እየሄዱ መሆኑን አመለክተዋል

በዚህ ታሪካዊ ችግኝ ተከላ ከዚህ ቀደም በተለየ መልኩ በጂኦ ሪፈረንስድ ወይም በሳተላይት በታገዘ ሁኔታ መርሀ ግብሩ ይከናወናል ብለዋል ፡፡

መርሀ ግብሩ የተመናመነውን የደን ሽፋን ለመመለስና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ተግባር ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል ፡፡

የከተማ ልማትን ቱሪዝም ዘርፍን ኢንዱስትሪ ዘርፉን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ፡፡

ባለፈት 5 አመታት ከታየው አንፃር ማህበራዊ ትስስርን በማጎልበት ረገድ ትልቅ ፋይዳም አለው ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታዋ ፡፡

የመገናኛ ብዙሀንም ስራውን ከተለያዩ ቦታዎች ለህዝብ እያደረሱ እንደሚገኝና ህብረተሰቡም በችግኝ ተከላው እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review