የአውሮፓውያኑ 2024 በታሪክ ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ ሞቃታማ ዓመት እንደሚሆን ተመራማሪዎች ገለጹ

AMN – ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

የአውሮፓውያኑ 2024 በታሪክ ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ ሞቃታማ ዓመት እንደሚሆን የኮፐርኒከስ የአየር ንብረት ለውጥ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

ተቋሙ እንደገለጸው በዚህ ዓመት በዓለም ዙሪያ ያለው አማካይ የሙቀት መጠን ከኢንዱስትሪ በፊት ከነበረው የሙቀት መጠን ከ1.5 ዲግሪ ሴልሽየሥ በላይ ይደርሳል፤ ይህም 2024ን ከፍተኛ ሙቀት የሚመዘገብበት ዓመት ያደርገዋል፡፡

ይህ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በአብዛኛው በሰው ልጆች እንቅስቃሴ ሳብያ በሚከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን እንደ ኤል ኒኖ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ሪፖርቱ በሚቀጥለው ሳምንት በአዘርባጃን የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ29) በፊት የማስጠንቀቂያ ጥሪ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review