የአደባባይ በዓላት ሀይማኖታዊ ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

You are currently viewing የአደባባይ በዓላት ሀይማኖታዊ ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

AMN- መስከረም 10/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ በወርሀ መስከረም አጋማሽ የምታስተናግዳቸው ግዙፍ የአደባባይ በዓላት ሀይማኖታዊ ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

አስተዳደሩ የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርጓል።

በዓላቱ ሲከበሩ አንድነትን በሚያጎለብት ፣ ፍቅርን በሚያፀና፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንዳለበት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ጥበቡ ደጀኔ (ዶ/ር) ተናግርዋል።

ሁለቱም ክብረ በዓሎች በአደባባይ የሚከበሩ ከመሆናቸው ባሻገር በርካታ የውጭ አገራት ቱሪስቶች የሚታደሙባቸው መሆናቸውን ያነሱት ሃላፊው የአዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ ያደረገው የኮሪደር ልማት ለበዓላቱ ተጨማሪ ድምቀት እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።

መስቀል እና ኢሬቻ ኢትዮጵያዊ እሴቶች የሚጎሉባቸው የሀገር መልኮች በመሆናቸው ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በጋራ እንሰራለን ብለዋል ነዋሪዎቹ።

በዓላቱ በድምቀት ተከብረው እንዲጠናቀቁ የከተማዋ ነዋሪዎች እስከአሁን ሲያደርጉት የነበረውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ ቀርቧል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review