AMN-የካቲት 5/2017 ዓም
የአዲስ አለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እና የኮንቬንሽን ማዕከል ለአፍሪካ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ተጨማሪ የመሰባሰቢያ ማዕከል ሆኗል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ዛሬ በተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ እየተሳተፉ ለሚገኙ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የአለምአቀፉ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም አምባሳደሮች በአዲስ አለም አቀፍ ኤግዚቢሽን እና የኮንቬንሽን ማዕከል የኢፌዴሪ ፕረዝዳንት ታየ አጽቀስላሴ በተገኙበት አውደ ርእይ መጎብኘታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ማምሻውን ደግሞ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ መታደማቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አመልክተዋል ።
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንግዶቻችን ሁለተኛ ቤታችሁ በሆነችው አዲስ አበባ የሚኖራችሁ ቆይታ ፍጹም ስኬታማ እና አስደሳች እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል::