የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በሰራቸው የሰላም እና ጸጥታ ስራዎች የመዲናዋን ሰላም ማስጠበቅ ተችሏል

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በሰራቸው የሰላም እና ጸጥታ ስራዎች የመዲናዋን ሰላም ማስጠበቅ ተችሏል

AMN – ታኅሣሥ 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ ባከናወናቸው የሰላም እና ጸጥታ ስራዎች የመዲናዋን ሰላም ማስጠበቅ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና በሸገር ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት መካከል ሰላም እና ጸጥታ በጋራ ከማስፈን አኳያ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች እና በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱ ቁልፍ ተግባራትን የሚገመግም መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በሁለቱ ከተሞች ቅንጅት የተከናወኑ ስራዎች የአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞችን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ቅንጅታዊ ስራዎቹ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ታላላቅ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ማስቻሉን ገልጸዋል።

በቅንጅት በመስራት የህዝብን ሰላም ማረጋገጥ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ፣ የህዝብን የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከር እና የሰላሙ ባለቤት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የውይይት መድረኩ በቅንጅታዊ አሰራሩ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ማስቀጠል በሚቻልበት እና የበለጠ አስተማማኝ ሰላም እና ጸጥታ ማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩርም ተመላክቷል፡፡

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review