የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት፡-
1. የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኃላ አጽድቋል።
2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ረቂቅ ደንብ አጽድቋል።
3. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኃላ የውሳኔ ሀሳቡን ማጽደቁን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡