የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ

AMN- መስከረም 30/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ የ2016 በጀት አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት ቅንጅታዊ ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሞሊቶ አባይነህ ተናግረዋል።

ይህም በተለይ ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት መስጠት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ያደርጋልም ተብሏል።

ቢሮው ከ15 በላይ ከሚሆኑ የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነትም አድርጓል።

ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የጋራ የሆነ ለውጥ ለማስመዝገብ እንደሚሰሩም የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review