AMN ሀምሌ 27/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮች ወቅታዊ የአዲስ አበባ ከተማን የፀጥታ ሁኔታን በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት በማድረግ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል ።
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባስተላለፋት መልዕክት በከተማችን ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ከዚህ በበለጠ አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ የሚጠብቁንን ሠላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተልዕኮን በቁርጠኝነት መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በመድረኩ የኢኮኖሚ ሪፎርሙን መነሻ በማድረግ ምርት መደበቅ፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪና መሰል ህገወጥ ድርጊት በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ የፀጥታ ሃይሉ የተልዕኮ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል።
አሁን ላይ በከተማው ያለውን ሰላም አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ በከተማችን የሚኖሩ ሁነቶችን ሰላምና ደኅንነት የማረጋገጥ አቅጣጫዎች ላይ መመሪያ ተሰጥቶ ውይይቱ መጠናቀቁን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል