AMN – የካቲት 22/2017 ዓ.ም
‘የአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ራዕይ መዲናችን አዲስ አበባ በአህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ኩነቶች መስተንግዶ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ማየት ነው’ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ‘ይህ ታላቅ ጉዞ መጀመሩ ለመላው ኢትዮጵያውን ከፍ ያለ ኩራት ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አለን’ ብለዋል፡፡