“የአገር መከላከያ ሰራዊት ዘመናዊ ሆኖ የአገርን ሰላም ማጽናት በሚችልበት መልኩ የተዋቀረ ነው”፡- የኤፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing “የአገር መከላከያ ሰራዊት ዘመናዊ ሆኖ የአገርን ሰላም ማጽናት በሚችልበት መልኩ የተዋቀረ ነው”፡- የኤፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ

የአገር መከላከያ ሰራዊት ዘመናዊ ሆኖ የአገርን ሰላም ማጽናት በሚችልበት መልኩ መዋቀሩን የኤፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

116ኛው የአገር መከላከያ ሰራዊት ቀን “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚጸና የድል ሰራዊት” በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ እተከበረ ነው፡፡

ቀኑን በማስመልከት የኤፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

መከላከያ ታሪኩን የሚያውቅ ታሪክ ጠገብ የአገር መጽናት የሰላም ምልክት መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

መከላከያ አላማው ሰላምን ማጽናት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደሙን የሚያፈሰው አጥንቱን የሚከሰክሰው የህይወት መስዕዋትነት የሚከፍለው ለሰላም ሲል ነው ብለዋል፡፡

መከላከያ ያለን ሰላም የጸናል የጠፋን ሰላም ይመልሳል የአገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ መስዕዋትነት ይከፍላልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ከኮሪያ ዘመቻ እስከ ሶማሊያ ለሁሉም ሰላም ማስከበር የህይወት መስዕዋትነት የከፈለ ነው ብልዋል፡፡

መከላከያ የአገርን ዳር ድንበር ከማስከበር አልፎ በተለያዩ የልማት ስራዎች በመሳተፍ የልማት እና የአንድነት በአጠቃላይ የአገር ምልክት በመሆን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

መከላከያ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምን ከየትኛውም የፖለቲካ ውግንና የጸዳ ለአገሩ ሰላም ብቻም ሳይሆን ለአፍሪካም ጭምር ኩራት የሆነ ተቋም ነው ሲሉም አመልክተዋል፡፡

መከላከያ በአደረጃጀቱ ዘመናዊ እንዲሆን መሰራቱን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ መከላከ በአየር በየብስና በባህር የተሟላ ቁመና እንዲኖረው ተደርጎ መዋቀሩን ተናግረዋል፡፡

መከላከያ አሁን ላይ ጠንካራ አደረጃጀት እንዲኖረው ተደርጎ መዋቀሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

መከላከያ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ እንዲሆን ተደርጎ ተዋቅሯል ያሉት ዶክተር ዐብይ ጠቅላይ ውጊያ ማቀድ ብቻ ሳይሆን የመፈጸም አቅሙም ከፍተኛ እንዲሆን ተደርጓ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በማንም ኃይል ተሸንፋ አታውቅም አሁንም አትሸነፍም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ማንንም ወራ አታውቅም አትወርምም ብለዋል፡፡

የ100 አመት ታሪክ ያለው መከላከያ ዓላማው መግደል እና ማጥቃት ሳይሆን አገርን ከጠላት መከላከል ተቀዳሚ ስራው ነው ብለዋል፡፡

መከላከያ አሁን ማንንም የማጥወቃትእቅድ የለውም ነገር ግን ለሰላም ሲል በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች በሰላም ማስከበር ተልእኮ ተሰማርቶ የሚያኮራ ገድል ፈጽሟል ወደፊትም ለሰላም ይሰራል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review