AMN – ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም
የአገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ተቋራጮችን አቅም በማሳደግ የአገርን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።
ይህ የተባለው የኮንስትራክሽን ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በምክክሩ የአገርን ዘላቂ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው የአገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ተቋራጮችን አቅም በማሳደግ መሆኑ ተነግሯል።
በመድረኩ በቀረበዉ ፅሁፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ለአገራዊ ምርት ዕድገት ከ20 እስከ 22 በመቶ ድርሻ እያበረከተ መሆኑ ተመላክቷል።
ሆኖም ከ60 በመቶ በላይ የአገሪቱን የካፒታል በጀት የሚጠቀመው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በብቁ የሰው ኃይል እጥረት፣ በአነስተኛ ፕሮጀክት አስተዳደር እውቀት፣ተቀናጅቶ ባለመስራት፣በብልሹ አሰራሮችና መሰል ችግሮች እየተፈተነ መሆኑ ተነግሯል።
መንግስት በልዩ ሁኔታ ከሚከታተላቸው ፕሮጀክቶች ውጪ በሌሎች የፕሮጀክት የመጓተት ችግሮች እንደሚስተዋሉም ነው በመድረኩ የተጠቀሰው።
ችግሮቹን ለመፍታት ከህግ ጋር የተያያዙ ክፍተቶችን ከማረም ጀምሮ ማበረታቻ መስጠት ላይ እንደሚተኮርም ተነግሯል።
በትዕግስት መንግስቱ