AMN- ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም
የአፍሪካ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች በቢሾፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አየር ሀይልን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ተገኝተዋል።
ለሶስት ቀን የሚቆየው የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን ዛሬ የጉባኤው ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አየር ሀይልን ጎብኝተዋል።
ጎብኚዎቹም በአየር ሀይል ቅጥር ግቢ የሚገኙትን የበረራ ትምህርት ቤት፣ ኤር ቤዝ፣ የሲሙሌተር ማዕከልንና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡