የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት የሥራ ድርሻ ምንድነው?

You are currently viewing የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት የሥራ ድርሻ ምንድነው?

AMN – የካቲት 5/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 13 ላይ እንደተጠቀሰው የሥራ አስፈፃሚው ምክር ቤት በህብረቱ የመሪዎች ስብሰባ በአባል ሀገራቱ የጋራ ጥቅም ላይ የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎች ተፈፃሚነትን ተከታትሎ የማስተባበር ሥራ የሚከውን ነው፡፡

-የስራ አስፈፃሚው ምክር ቤት ስብሰባ ከመሪዎች ስብሰባ ቀደም ብሎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄድ ነው

-ሁሉም አባል ሀገራት በስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ውስጥ ይሳተፋሉ

የሥራ አስፈፃሚው ምክር ቤት ዋና ተግባራት ፦

-የጉባዔውን ስብሰባ ማዘጋጀት እና በጉባዔው ላይ ከውሳኔ የሚደረስባቸውን አጀንዳዎች ማቅረብ

-በጉባዔው የሚሾሙትን ኮሚሽነሮች መምረጥ

-ከቀጣናዊ የኢኮኖሚክ ማህበረሰቦች (RECs)፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB)፣ ከሌሎች የአፍሪካ ተቋማት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ጋር ትብብር እና ቅንጅትን ማጠናከር

-በአፍሪካ ህብረት እና በአፍሪካ አጋሮች መካከል ትብብርን የሚያጠናክሩ ፖሊሲዎችን መወሰን

-በኮሚሽኑ መዋቅር፣ ኃላፊነትና ሥልጣን ላይ ምክረ ሀሳቦችን መስጠት

-የፆታ እኩልነት በሁሉም የአፍሪካ ህብረት ፕሮግራሞች ውስጥ እንዲተገበር ማበረታት

በወርቅነህ አብዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review