AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በራሷ ተነሳሽነት ያዘጋጀችው የመጀመሪያው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ጉባኤው “አፍሪካ በጠንካራ አንድነት፣ ለሁለንተናዊ ፀጥታና ሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ታውቋል።
በጉባኤው የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ወታደራዊ አታሼዎች፣ በወታደራዊ ጉዳይ ላይ የተሰማሩ ተመራማሪዎች ይሳተፋሉ።
በጉባኤው አፍሪካውያን በጋራ ጉዳዮቻቸው በመምከር መፍትሔ የሚያስቀምጡበትና ወንድማማችነታቸውን የሚያጠናክሩበት መሆኑም የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ትላንት በሰጠው መግለጫ ተመልክቷል፡፡