የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የፈረንሳይ ስትራቴጂካዊ ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የፈረንሳይ ስትራቴጂካዊ ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
  • Post category:ዓለም

AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽንና የፈረንሳይ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ምክክር በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በውይይቱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማትና የአውሮፓና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ጂያን-ኖኤል ባሮት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ኅብረትና ፈረንሳይ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የሁለትዮሽ አጋርነትና የትብብር ማዕቀፎች አስመልክቶ ውይይት ይደረጋል።

ሁለቱ ወገኖች በባለብዝኃ ወገን ዲፕሎማሲ ያላቸው ግንኙነትም ሌላኛው የውይይቱ አጀንዳ ነው።

ምክክሩ የሁለቱን ወገኖች አጋርነት ይበልጥ ማጠናከርን ያለመ ነው።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማትና የአውሮፓና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጂያን-ኖኤል ባሮት ውይይቱን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

ሰላም፣ደኅንነት፣ኢኮኖሚ፣የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ትምህርት ከአፍሪካ ኅብረትና የፈረንሳይ የትብብር መስኮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review