AMN – ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም
የአፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን/ኢመደአን/ ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሮቹ ጉብኝት ያደረጉት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ የመከላከያ የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ነው።
ለመከላከያ ሚኒስትሮቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉት የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት፣ ተቋሙ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነቷንና ዲጂታል ሉዓላዊነቷን ለመጠበቅ የሚያስችል አይበገሬ የሳይበር አቅም ለመገንባት እያደረገ ስላለው ስራ ሰፊ ገለጻ ማድረጋቸውን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።