የአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት፣ የገንዘብና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት፣ የገንዘብና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ እየተካሄደ ነው

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ያዘጋጀው 57ኛው አህጉራዊ የኢኮኖሚ ልማት፣ የገንዘብ እና የፕላን ሚኒስተሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው በሚኒስትሮች ደረጃ ከመጋቢት 8/2017 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል።

በባለሙያዎች ደረጃ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ፔድሮ፣ የመንግስታቱ ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም የሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

ጉባኤው “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን የሚያፋጥኑ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን መቀየስ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የአፈፃጸም ሂደትና የቀጣይ ተግባራት ላይ ምክክር ይደረጋል።

በተጨማሪም የአህጉሪቱ የምግብ ዋስትና፣ የዲጂታል እና የኃይል ትራንስፎርሜሽን ሥርዓትን ማሳለጥ የሚያስችሉ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

ዛሬ በባለሙያዎች ደረጃ የተጀመረው አህጉራዊው የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ እስከ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

በሚኒስትሮች ደረጃ ደግሞ ከመጋቢት 8 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ የፖሊሲ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review