የአፍሪካ ፍልሰተኞችን መጠን በአግባቡ ለማወቅና የፖሊሲ መነሻ ለማድረግ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ እየተከናወነ ነው- የአፍሪካ የፍልሰት ኦብዘርቫቶሪ ዳይሬክተር ናምራ ነገም (ዶ/ር)

You are currently viewing የአፍሪካ ፍልሰተኞችን መጠን በአግባቡ ለማወቅና የፖሊሲ መነሻ ለማድረግ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ እየተከናወነ ነው- የአፍሪካ የፍልሰት ኦብዘርቫቶሪ ዳይሬክተር ናምራ ነገም (ዶ/ር)

AMN-የካቲት 9/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ፍልሰተኞችን መጠን በአግባቡ ለማወቅና የፖሊሲ መነሻ ለማድረግ የሚያስችል ዳታ ቤዝ ተደራጅቶ መረጃዎችን የማደራጀት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአፍሪካ የፍልሰት ኦብዘርቫቶሪ ዳይሬክተር ናምራ ነገም (ዶ/ር) ተናገሩ።

ዳይሬክተሯ ከ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በአፍሪካ ዜጎች ፍልሰት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአፍሪካውያን ፍልሰተኞች ቁጥር በቅጡ የማይታወቅ በመሆኑ የተለያዩ ሀይሎች ለፖለቲካ አላማ ሲጠቀሙበት ይታያል ያሉት ዳይሬክተሯ ይሁን እንጂ ፍልሰተኞቹ ለሚሄዱባቸው ሀገሮች ልማት እና እድገትም የማይናቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ብለዋል።

በመሆኑም አፍሪካ ወደ ሌሎች ዓለማትም ይሁን በራሷ በአህጉሯ ውስጥ የሚደርግ ፍልሰትን እና የፍልሰተኞች መጠንን ለይታ ማወቅ እንደሚገባት ገልጸዋል።

በዚህም በተለያዩ አካላት ለተለያየ አላማ እየተዛባ የሚቀመጠውን የፍልሰተኞች ቁጥር በትክክል ማወቅ እና ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል ብለዋል።

በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ሀኪሞች እና መሀንዲሶች እንዲሁም ሌሎች ሞያተኞች ወደ ሌሎች አለማት እንደሚፈልሱ ያነሱት ዳይሬክተሯ እነዚህን ሞያተኞች ለማብቃት አፍሪካ ከፍተኛ ወጪን ያወጣችባቸው ቢሆንም ትርፏ ኪሳራ ነው በአንጻሩ የፍልሰት ተቀባዮቹ አለማት ትርፋማ ይሆናሉ ብለዋል።

ከዚህ አንጻር አፍሪካ ካሰለጠነቻቸው ሞያተኞች ተጠቃሚ እንድትሆን ህጋዊ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍልሰትን ተግባራዊ ለማድረግ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ንግግር በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ህጋዊ ፍልሰትን በማጠናከር ውጭ ያሉ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ከሚልኩት የሬሚታንስ ገንዘብ እንዲሁም በስምምነት ከሚካሄድ የሰው ሀይል የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ለአፍሪካ ልማት የሚውል ሀብት ማግኘት ስለሚቻል በዚህ ረገድ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል ዳይሬክተሯ።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review