AMN-መስከረም 21/2017 ዓ.ም
አብሮነትና ፍቅር የሚንጸባረቅበትን የኢሬቻን በአል ስናከብር የቆየዉን አብሮነታችንን አጉልተን በማዉጣት መሆን አለበት ሲሉ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አስገነዘቡ።
የዘንድሮዉን የኢሬቻ በአል ዝግጅትን አስመልክቶ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሲካሄድ የቆየዉ ዉይይት ማጠቃለያ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል ።
በማጠቃለያው ላይ አመታዊዉ የኢሬቻ በአል ትዉፊቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ይከበር ዘንድ በከተማዋ እና በከተማዋ ዙሪያ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል ተብሏል ።
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ባስተላለፉት መልእክትም አብሮነትና ፍቅር የሚንጸባረቅበትን የኢሬቻ በአል ስናከብር የቆየዉን አብሮነታችንን አጉልተን በማዉጣት መሆን አለበት ብለዋል።
የመዝጊያ ስነ ስርአቱ ላይ በበአሉ ዙሪያ በምሁራን ሰነዶች ቀርበዉ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የኦሮሞ ባህልን የሚያሳዩ የተለያዩ ባህላዊ ምግቦችም ለእይታ ቀርበዋል ።
በአለማየሁ አዲሴ