የኢሬቻ በዓል ቂም እና ጥላቻ የሚወገዝበት ፍቅርና አንድነት የሚወደስበት በዓል በመሆኑ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እንሰራለን – የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ

You are currently viewing የኢሬቻ በዓል ቂም እና ጥላቻ የሚወገዝበት ፍቅርና አንድነት የሚወደስበት በዓል በመሆኑ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እንሰራለን – የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ

AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን በክፍለ ከተማ ደረጃ በፓናል ውይይት እና በልዩ ልዩ ባህላዊ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።

ኢሬቻ ቂም እና ጥላቻ የሚወገዝበት ፍቅርና አንድነት የሚወደስበት በዓል በመሆኑ ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚሰራ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ንጋቱ ዳኛቸው ገልጸዋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሙሉጌታ ጉሉማ በበኩላቸው፣ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት እና ፈጣሪውን የሚለምንበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከተማ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች ፣ ሃደ ሲንቄዎች ፣ ወጣቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በፓናል ውይይቱ ላይ እየተሳተፉ ነው።

የፊታችን ቅዳሜ የኢሬቻ በዓልን ለማክበረ በክፍለ ከተማው በኩል የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review