የኢሬቻ በዓል የበለጠ እንዲያድግና እንዲጎለብት የዘርፉ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

You are currently viewing የኢሬቻ በዓል የበለጠ እንዲያድግና እንዲጎለብት የዘርፉ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

AMN-መስከረም 20/2017 ዓ.ም

የኦሮሞ ህዝብ መገለጫ የሆነውን የኢሬቻ በዓል የበለጠ እንዲያድግና እንዲጎለብት የዘርፉ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ፡፡

በኢሬቻ በዓል ላይ ያተኮረው 38ኛው ጉሚ በለል “ኢሬቻ ለባህል ህዳሴያችን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ በኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና በኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በውይይቱ ላይ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን እና የተለያዩ እንግዶች እየታደሙ ይገኛሉ።

የኦሮሚያ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሩ፣ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የበዓሉ ታዳሚ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የኢሬቻ በዓል ከዚህ በተሻለ መልኩ እንዲያድግ ምሁራን እና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተለይም የዓሉን እውነተኛ ገፅታ የሚያሳዩ እና ባህላዊ ትውፊቱን የሚያንፀባረቁ ሁነቶች ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ስላለፈው የሚያመሰግንበት ስለሚመጣው የሚለምንበት አኩሪ ባህል መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

በበዓሉ የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ እያደገ ከመምጣቱም በተጨማሪ የውጭ ዜጎች መዳረሻ እየሆነ መምጣቱም ተገልጿል።

በበዓሉ ላይ የሚነሱ የተንሸዋረሩ ምልከታዎችን ማረቅ እና ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ ማድረግ ይገባል ተብሏል።

በሐብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review