የኢስዋቲኒ ንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊ ብሔራዊ ቤተመንግሥትን ጎበኙ

You are currently viewing የኢስዋቲኒ ንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊ ብሔራዊ ቤተመንግሥትን ጎበኙ

AMN – የካቲት 9/2017 ዓ.ም

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የኢስዋቲኒ ንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊን ብሔራዊ ቤተመንግሥትን አስጎብኝተዋቸዋል።

ንጉሥ ምስዋቲ ሣልሳዊ በዚሁ ወቅት፥ በፕሬዝዳንቱ ግብዣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ቤተመንግሥቱ በርካታ ታሪኮችን በውስጡ የያዘ መሆኑንም ተመልክቻለሁ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ቀደምት አፍሪካውያን መሪዎች ለአፍሪካ አንድነት የመከሩበት የጋራ ማዕድ የቆረሱበት፣ በጥቅሉ የአፍሪካን እጣ ፈንታ የሚወስኑ ትልልቅ ውሳኔዎችን ያሳለፉበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ይህም ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴን ጨምሮ የኢትዮጵያ መሪዎች ለአፍሪካ ያደረጉትን ጉልህ አስተዋፅኦ የሚዘክር መሆኑን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review