የኢትዮጵያና የናይጀሪያ መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ለመሥራት በሚያሥችሉ ጉዳዮች በናይጀሪያ እየመከሩ ነው

AMN – ታኅሣሥ – 11/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሳ የተመራ ልዑክ በናይጀሪያ ፌደራል ሪፐብሊክ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝቶ በሁለትዮሽ ወታደራዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዬ ነው።

ውይይቱ የኢትዮጵያን እና የናይጀሪያን የመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ፕሮፌሽናሊዝም በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ ለማሳደግ ተግባር ላይ ማዋል በሚችሉ የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

የወታደራዊ ልዑኩ ጉብኝት በቀጣይ የሁለቱን ሃገራት የመከላከያ ሠራዊት መጥቀም በሚያስችሉ የትምህርት ፣ የስልጠና ፣ የልምድ እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላከታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review