የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ወዳጅነት በጠንካራ የልማት ትብብር ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል፡-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ታኅሣሥ 13/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ወዳጅነት በጠንካራ የልማት ትብብር ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

አቶ ተመስገን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በኢትዮጵያ የተገኘውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ትብብር ከሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት ብለዋል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣትም ይህ ዲፕሎማሲያዊ ትብብራችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንድ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የፈረንሳይ መንግስት በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያን እና በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት እድሳት ላደረገልን ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ በመምጣቶ ክብር ይሰማናል፡፡ አዲሲቷን ኢትዮጵያን እንደ አዲስ ስለጎበኟትም እናመሰግናለን ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review