የኢትዮጵያን ወጪና ገቢ ንግድ የሚያሳልጥ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶታል- ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

You are currently viewing የኢትዮጵያን ወጪና ገቢ ንግድ የሚያሳልጥ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶታል- ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ማሳለጥ የሚያስችል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አቅምን የማሳደግ ሥራ ትኩረት እንደተሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ ፈጣን ሁሉን አቀፍ ዕድገት እያስመዘገበ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን የኢኮኖሚ ግንባታ የሚሳካው ለምርቶች ዝውውርና የገበያ ሰንሰለት ብቁ የማጓጓዣ ስርዓት በመፍጠር ነው ብለዋል።

ሎጂስቲክስ የኢኮኖሚ የደም ስር ነው ያሉት አቶ አወል፤ መንግሥት እያደገ የመጣውን የገቢና ወጪ ንግድ የሚያሳልጥ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አቅም በመገንባት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈጣንና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ዕውን ለማድረግ ለዘርፉ መሰረተ-ልማት ግንባታ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል።

የአፋር ክልል የገቢና ወጪ ንግድ መተላለፊያ እንደመሆኑ በአካባቢው ያሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ደህንነት እንዲጠበቅ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም እንደ ሀገር የወጪና ገቢ ንግዱን ለማሳለጥ አጋዥ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

መንግሥት የሎጂስቲክስ ዲጅታላይዜሽን እና የፍጥነት መንገዶችን እየገነባ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

በቀጣይም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ላይ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review