የኢትዮጵያን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲዎች የሚያስተዋውቅ ጆርናል ይፋ ተደረገ

You are currently viewing የኢትዮጵያን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲዎች የሚያስተዋውቅ ጆርናል ይፋ ተደረገ

AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም

የውጪ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት የኢትዮጵያን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ማዕቀፎች ለማስተዋወቅና ለማስረዳት የሚያግዝ ”ዲስኮርስ” የተሰኘ ጆርናል ይፋ አድርጓል።

ይህ ጆርናል ኢኒስቲትዩቱ የሚያካሄዳቸው ጥናትና ምርምሮች ጥቅም ላይ እንዲውሉም የሚያስችል ነው ተብሏል።

የውጪ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ (ዶ/ር) በመርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ለዘመናት የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረቷን ተናግረዋል።

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነቷን የሚያጎሉ በርካታ ተግባራት ማከናወኗን ገልጸው፣

ይህንን አቅሟን ይበልጥ የማጠናከር እና ተደራሽነቷን የማስፋት ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።

ኢኒስቲትዩቱ ለዘርፉ አጋዠ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማካሔድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እያደረገ እንደሚገኝ መግለፃቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

ይፋ የተደረገው ጆርናል ኢትዮጵያን ይበልጥ ለማስተዋወቅ፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር፣ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች በጥናት እና ምርምር በተደገፉ መረጃዎች ተደራሽ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንዳለውም አመላክተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ነባር አምባሳደሮች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች እና የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላተ ተገኝተዋል።

ጆርናሉ በየስድስት ወሩ እንደሚታተም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review