የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ለአሻም ሚዲያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

You are currently viewing የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ለአሻም ሚዲያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

AMN-መስከረም 29/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ለአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የመጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጥቷል ፡፡

ባለስልጣኑ በላከው ደብዳቤ አሻም የቴሌቪዥን ጣቢያ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ 1238/2013 እና ሌሎች የአገሪቱ ሕጎችን እንዲሁም የፈቃድ ውል ግዴታዎችን አክብሮ ለመስራት ከባለስልጣኑ ፈቃድ ወስዶ በስርጭት ላይ እንደሚገኝ አስታውሶ ይሁን እንጂ ጣቢያው ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎችን፣ግጭት አባባሽ ዘገባዎችን፣ የሕዝብን ኣብነሮት የሚሸረሽሩና የአገርን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዱ መረጃዎችን በቂ ማጣራትና ምክንያታዊ ጥረት ጎያደርግ በተደጋጋሚ ማሰራጨቱን አረጋግጠናል ብሏል፡፡

የቴሌቪዥን ጣቢያው ከዚህ ቀደም ባሰራጨው ግጭት ተኮር እና ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ ከድርጊቱ ኣንዲቆጠብ በተደጋጋሚ በባለስልጣኑ የጽሁፍና የቃል ማሳሰቢያ ሲሰጠው መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ጣቢያው በባለስልጣኑ የተሰጠውን የጽሁፍና የቃል ማሳሰቢያ ባለማክበር የአገሪቱን ሕጎች የሚጥሱ ይዘቶችን በማሰራጨት ላይ እንደሚገኝም ገልጧል፡፡

ጣቢያው ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገየጊዜው የሚሰራጩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ወደ መደበኛ ሚዲያ በማምጣት ኅብረተሰቡን ለማደናገር ጥረት ሲያደርግ ይስተዋላልም ብሏል ባለስልጣኑ በደብዳቤው ፡፡

በመሆኑም አሻም ቴሌቪዥን ጣቢያ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ 1238/2013 መሰረት የሕግ የበላይነትን ኣክብሮ በገባው የፈቃድ ውል ግዴታ ከመስራት አንጻር በፈጸመው ተደጋጋሚ ጥሰት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review