የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ራይድ ትራንስፖርት ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ራይድ ትራንስፖርት ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ራይድ ትራንስፖርት ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዲጅታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ወጋየሁ ገ/ ማርያም እንደተናገሩት ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የተደረገው ስምምነት በተለያዩ የዲጅታል አገልግሎቶች የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም ክፍያን ማሳለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል።

የራይድ ትራንስፖርት የሽያጭና ማርኬቲንግ ሃላፊ አቶ ዘላለም ጌታቸው በበኩላቸው ስምምነቱ ከ70 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችና 5 ሺህ ሠራተኞችን ይዞ በሚሠራው ራይድ ትራንስፖርት በዲጅታል ስርአቱ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review